Fana: At a Speed of Life!

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አቋርጦት የነበረውን መደበኛ የህክምና አገልግሎት ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮቪድ 19 ህክምናን እና መደበኛ ህክምናዎችን በአንድነት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ።

ሆስፒታሉ ሙሉ ለሙሉ የኮቪድ 19 ታካሚዎችን ተቀብሎ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፥ ቀድሞ ይሰጣቸው የነበሩ የህክምና አገልግሎቶችን በአቅራቢያው ወደሚገኙ ጤና ጣቢያዎች አዘዋውሮ አገልግሎት ሲሰጥ ቀይቷል።

ሆስፒታሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ አሁን ላይየኮቪድ ህክምና እና የመደበኛ ህክምና አገልግሎት በጣምራ ለመስጠት ሊጀምር ነው።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ታምሩ አሰፋ፥ የኮቪድ 19 ፅኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ቁጥር እንደተጠበቀው ባለመሆኑ አብዛኛው ታካሚ በቤቱ ራሱን በመንከባከብ ወይም በሌሎች ማቆያ ቦታዎች እየታከመ በመሆኑ እንዲሁም በሌሎች ህመሞች ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የኮቪድ ህክምና እና የመደበኛ ህክምና አገልግሎት በጣምራ ለመስጠት እንዳስፈለገ ተናግረዋል።

ጥምር አገልግሎቱን ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውን የገለጹት ዋና ስራ አስኪያጁ፥ ባለሙያዎች የተዋቀሩ ሁለት ኮሚቴዎች መቋቋማቸውን ገልጸዋል።

የሆስፒታሉ ሜዲከል ዳይሬሬተር ዶክተር መታሰቢያ መስፍን፥ በሆስፒታሉ የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት መጀመሩን ገልፀው፤ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ሙሉ በሙሉ ወደስራ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኮቪድ ህክምና ሆስፒታሉ ባስገነባው የፊልድ ሆስፒታል እንደሚሰጥም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.