Fana: At a Speed of Life!

መንግሥታት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ሊያበረታቱ፣ ሊደግፉና እውቅና ሊሰጡ ይገባል – አንቶኒዮ ጉተሬዝ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥታት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ሊያበረታቱ፣ ሊደግፉና እውቅና ሊሰጡ ይገባል ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሳሰቡ።
ዛሬ በአለም አቀፍ ደረጃ የበጎ ፈቃኞች ቀን እየተከበረ ነው።
ዋና ጸሐፊው አንቶሪዮ ጉተሬዝ ቀኑን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ÷መንግሥታት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ሊያበረታቱ፣ ሊደግፉና እውቅና ሊሰጡ ይገባል ብለዋል።
በጎ ፈቃደኞች ለሚሰጡት አገልግሎት እውቅናና ድጋፍ መስጠት ቀጣይነት ላለው የልማት ስኬት ወሳኝ ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል።
በዚህም ያለመታከት በጎ ፈቃደኞች ለሚሰጡት አገልግሎት “ልባዊ ምስጋናችንን ልናቀርብላቸው ይገባል” ብለዋል።
የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በማንኛውም ጉዳይ ላይ በነጻ የሚሰጥ አገልግሎት ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በንጉሣዊው ስርኣት በስካውት ማኅበር ተጀምሮ፣ በዕድገት በሕብረት ዘመቻ መሰረቱን ጥሎ በአሁኑ ወቅት በመንግስታዊ ተቋምና በማሕበር እንዲሁም በግል ተነሻሽነት እየተከናወነ የሚገኝ ተግባር ነው ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.