Fana: At a Speed of Life!

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እኩይ ተልዕኮ ተሸክሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው የህወሓት ሃይል ተወግዶ መከበሩ ልዩ ያደርገዋል – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ህዝቦችን በማናከስ እኩይ ተልዕኮ ተሸክሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው የህወሓት ሃይል ተወግዶ መከበሩ ልዩ እንደሚያደርገው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

15ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የሃገር አቀፍ ሲምፖዚየም መርሐግብር እየተካሄደ ነው።

በመርሐግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ራሳቸውን ችለው በልዩ ውበት የሚፈሱ ወንዞች ናቸው ብለዋል።

ይህ ውበታቸው ሕብረ ብሔራዊነትን የያዘ የአንድነት መገለጫ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በዓሉም የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ውበት ማሳያ መሆኑንም አንስተዋል።

የህወሓት ቡድንን እኩይ ሃይል ለማስወገድ ዋጋ ለከፈሉ የጸጥታ ሀይሎችና ዜጎች ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጥፋት አላማ የሚያራምዱ አካላትን እድል ሳይሰጡ ማክሸፍ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

አፈ ጉባኤው የሕግ የበላይነትን ማስከበር ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማስቀጠልና ሕብረ ብሔራዊነት አንድነትን ለማስጓዝ ቀዳሚ ተግባር መሆኑንን አውስተዋል።

በዚህም ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመጣልና የህዝቦችን አንድነት ለማፍረስ በተንቀሳቀሰው የህወሓት ሀይል ላይ የህግ ማስከበር እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል።

የጥፋት ቡድኑን ለማስወገድ መስዋዕትነት ለከፈሉ ምስጋና ይገባቸዋልም ነው ያሉት አፈ ጉባኤው።

ፍትሐዊ ተጠቃሚነትትን ለማረጋገጥ ከሚያለያዩ ሐሳቦች በመራቅ በጋራ እሴቶች ላይ መስራት እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

በመርሐግብሩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮችና የብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች እና የሐይማኖት መሪዎች ተገኝተዋል።

መርሐግብሩ በጁንታው ቡድን ክህደት ለተፈጸመባቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት የህሊና ጸሎት በማድረግ ነበር የተጀመረው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.