Fana: At a Speed of Life!

ኢ/ር ታከለ ኡማ ህገወጥ የቤቶች ግንባታ ላይ በሚወሰደው እርምጃ ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2012(ኤፍቢሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢጅነር ታከለ ኡማ ህገወጥ የቤቶች ግንባታ ላይ በሚወሰደው እርምጃ ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አደረጉ፡፡
 
የህገወጥ ግንባታዎችን በተመለከተ የተደረገው ጥናት እና ህግን የማስከበር እርምጃው ማስፈጸሚያ መንገዶች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡
 
በቅርብ ጊዜያት እየተስፋፋ የመጣውን ህገወጥ የመሬት ወረራና ግንባታ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን በቅርብ ቀናትም ወደ ትግበራ እንደሚገባ ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
 
እርምጃው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 116 ወረዳዎች ላይ የሚወሰድ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ፖሊስና የከተማዋ አጎራባች ወረዳዎች ይሳተፋሉ ተብሏል።
 
በየወረዳው በህገወጥ መልኩ የተገነቡ ቤቶችን የመለየት ስራም እየተሰራ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
ከውይይቱ በኋላ በጉዳዩ ላይ መግለጫ የሰጡት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አራጋው ህገወጥ ግንባታዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ህግን ከማስከበር ጋር ብቻ የተያያዘ እንደሆነ ገልጸዋልⵆ
 
ከዚህ በኋላ በሚኖሩ ጊዜያትም የከተማ አስተዳደሩ ቀድሞ የመከላከል ስራዎች ላይና ህገወጦች ላይ ጠንካራ እርምጃ የመውሰድ ተግባሩ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት አሳውቋልⵆ
 
ከህገወጥ ግንባታው ጋር የተያያዙ የስራ ኃላፊዎችም ይሁን የተለያዩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጻልⵆ
 
ከህገወጥ ግንባታዎች በተጨማሪ ለገነቡት ግንባታ በህገወጥ መንገድ የተገኘ ማስረጃ ያገኙ ግለሰቦች ላይ ማጣራት እየተደረገ እንደሆነ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.