Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ግብር ከፋዮች ያቀረቡትን 209 ሃሰተኛ ደረሰኝ መርምሮ ውድቅ በማድረግ ከ134 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተቻለ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 29 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግብር ከፋዮች ያቀረቡትን 209 ሃሰተኛ ደረሰኞች በባለሙያዎች መርምሮ ውድቅ በማድረግ ከ134 ሚሊየን ብር በላይ የተጭበረበረ የመንግስት ገቢ እንዲከፈል ማድረግ መቻሉን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ገለጸ።
በቢሮው የግብር እቅድና ጥናት የስራ ሂደት ሃላፊ አቶ አትንኩት በላይ ለኢዜአ እንደተናገሩት÷ በክልሉ ጠንካራና ታማኝ ግብር ከፋይ ማህበረሰብ ለመፍጠር በየደረጃው የማስተማርና ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተከናወነ ነው።
የግብር አሰባሰቡን በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ከማድረግ ባለፈም ግብር ስወራና ማጭበርበርን ለመከላከል በተደረገው ጥረት ባለፉት ወራት 267 ግብር ከፋዮች ጥፋተኛ ሆነው መገኘታቸውን አስረድተዋል።
ህገ ወጥ ደረሰኝ መጠቀም፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ አለመቁረጥ፣ ገቢን አሳንሶ ማሳወቅ፣ ወጪን ማብዛትና ግብር ማጭበርበር የፈጸሟቸው ጥፋቶች መሆናቸውን ሃላፊው አመላክተዋል።
ግለሰቦቹን በፈጸሙት ጥፋት ልክ በህግ ለመጠየቅ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝም ተናግረዋል።
58 ግብር ከፋዮች ደግሞ ያጭበረበሩትን 8 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር ለመንግስት ገቢ በማድረግ ጉዳያቸው በህግና አስተዳደራዊ ጉዳይ ታይቶ እንዲቀጡ ተደርጓል ብለዋል።
የግብር ስወራና ማጭበርበርን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀው÷ ግብር መሰወር ሀገርን የመዝረፍ ወንጀል በመሆኑ ግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ይህንን በመገንዘብ በሰራውና ባገኘው ገቢ ልክ የሚጠበቅበትን ግብር መክፈል እንዳለበት ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.