Fana: At a Speed of Life!

በአርሲ ዞን የመጀመሪያው የግብርና ባዛርና የገበያ ትስስር ኤግዚቢሽን እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአርሲ ዞን የመጀመሪያው የግብርና ባዛርና የገበያ ትስስር ኤግዚቪሽን እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ የግብርና ውጤቶች፣ ቴክኖሎጂዎች፣ ግብአቶች ከአምራቹ ወደ ገዢው በቀጥታ የሚቀርቡበት ነውም ተብሏል።

አምራቾች ቀጥታ ለሸማቾች ምርቶቻቸውን ማቅረባቸውም የሽያጭ ሰንሰለቱን በማሳጠር የዋጋ ውድነትን የሚቀንስ እንዲሁም ለአርሶ አደሩ የገበያ ትስስርን የሚፈጥር መሆኑን የአርሲ ዞን ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አባቡ ዋቆ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ሃላፊው መርሃ ግብሩ በዞኑ ለመጀመሪያ ጊዜ መዘጋጀቱን ገልፀው፤ ከዚህ በፊት ይነሱ የነበሩ የገበያ ትስስር ችግሮችን ይፈታል ብለዋል።

በግብርና ባዛርና ኤግዚቢሽኑ የግብርና ቴክኖሎጂ አምራቾች፣ የፀረ አረምና ፀረተባይ አምራች ኩባንያዎች፣ ማህበራት እና አርሶ አደሮች ምርቶቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን በዞኑ የሚገኙ ወረዳዎችም ተሳታፊ ሆነዋል።

መርሃ ግብሩ ለ3 ቀናት ይቀጥላልም ነው የተባለው።

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.