Fana: At a Speed of Life!

በህዳር ወር ከወጪ ንግድ 190 ነጥብ 73 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት አመቱ በህዳር ወር ከወጪ ንግድ 190 ነጥብ 73 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከግብርና፣ ከማምረቻው ዘርፍ እና ከማዕድን ውጤቶች 289 ነጥብ 15 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 190 ነጥብ 73 ሚሊየን ዶላር ወይም 65 ነጥብ 96 በመቶ ማሳካት ተችሏል።

ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በቅናሽ ያሳየ ሲሆን፥ የተፈጥሮ ሙጫና ዕጣን እንዲሁም አበባ እና ኤሌክትሪክ ከእቅድ በላይ አፈጻጸም ታይቶባቸዋል ተብሏል።
መረጃው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.