Fana: At a Speed of Life!

የጣልያናዊው እግርኳስ ተጫዋች ፓውሎ ሮሲ ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ጣልያን ዓለም ዋንጫን እንድታነሳ ካስቻሏት ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው ፓውሎ ሮሲ ህይወቱ አለፈ፡፡

የ64 ዓመቱ ፓውሎ ሮሲ ጣልያን በ1982 የዓለም ዋንጫን ስታነሳ ብሔራዊ ቡድኑን እየመራ ለድል ካበቁት መካከል አንዱ ነው፡፡

የሮሲን ህልፈት ባለቤቱ ፌዴሪካ ካፔሌቲበኢንስታግራም ገጽዋ ይፋ አድርጋለች፡፡

እስካሁን የህልፈቱ መንስዔ ምን እንደሆነ ይፋ ባይረደግም የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ረዘም ላለ ጊዜ ህመም ላይ ቆይቶ እንደነበረ ነው የዘገቡት፡፡

ሮሲ በ1982ቱ ውድድር ኮከብ ግብ አስቆጣሪና የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች እንደነበር ይታወሳል፡፡ አብዛኞቹ ደጋፊዎቹ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ብራዚል ላይ ሃትሪክ በመስራት ከውድድር ያስወጣበትን ወቅት የማይረሳ ነው ሲሉ ይናገራሉ፡፡

ሮሲ ከዚህ ቀደም የጨዋታ ውጤት ማጭበርበር በሚል ለሁለት ዓመታት ከእግርኳስ ታግዶ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

በ2004 በብራዚላዊው ፔሌ አማካኝነት ከምንጊዜም 125 ምርጥ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ተብሎ ተመርጧል፡፡

ከእግርኳስ ከተገለለ ከ1980ዎቹ መጨረሻ በኋላ ለስካይ፣ ሚዲያሴት እና ራይ ለተባሉ መገናኛ ብዙኀን ተንታኝ በመሆን ሰርቷል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል

https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.