Fana: At a Speed of Life!

ህብረተሰቡ በየአካባቢው የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ የአረንጓዴ አሻር መርሃግብሩን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 4 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ህብረተሰቡ በየአካባቢው የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ የአረንጓዴ አሻር መርሃግብሩን ውጤታማ ማድረግ ይገባል ሲሉ ገለጹ።
የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ እና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በክልሉ የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ መርሃግብር አካሂደዋል።
በዚሁ ወቅት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ ÷ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት እንፀዲጸቁ እንክብካቤ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ለዚህም የበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች እና የሚመለከታቸው አካላትን በማሳተፍ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች እየተገኘን ለተተከሉ ችግኞች እንክብካቢ በማድረግ የማነቃቃት ስራ እያከናወንን እንገኛለንም ነው ያሉት ።
በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ከሚገኘው ተግባር ጎን ለጎን ለችግኞች እንክብካቤ በማድረግ የዲሞክራሲ፣ የሰላም እና የልማት ጠንቅ ሊሆኑ የሚችሉ አረሞችን እየነቀልን ለመሄድ የሚያችል ተግባርን እየፈፀምን እንገኛለን ብለዋል።
በተለይም በቀጣዮቹ ወቅቶች ችግኞች እንዳይደርቁ ከማድረግ አንፃር ህብረተሰቡ በየአካባቢው የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ የሀገራዊ አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ውጤታማ ማድረግ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በመርሃግብሩ ከተሳተፉት መካከል የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊዋ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም በበኩላቸው÷ ክረምቱ መጠናቀቁን በማመላከት በተለይም በቀጣዮቹ ወቅቶች የተከልናቸው ችግኞች እንዳይደርቁና የታለመላቸውን ግብ እንዲመቱ ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
እንደ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በበጋው የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎትም ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በትኩረት ይሰራልም ሲሉ ተናግረዋል።
በክረምት የተከላቸው ችግኞችን በዘላቂነት እንዲፀድቅ እንክብካቤ እያደረገ መሆኑን የገለፀው ደግሞ በእለቱ ከተሳተፉ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች መካከልም ከአሚር ኑር ወረዳ ነዋሪው ወጣት ስንታየሁ ተሾመ ነው።
በቀጣይም እሱና ሌሎች የክልሉ ወጣቶች በአካባቢያቸው ሰላምን ከማስፈን ተግባር ጎን ለጎን ለተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ እንደሚያደርጉመናገራቸውን ከሀረሪ ክልላዊ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.