Fana: At a Speed of Life!

በአምስት ወራት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአምስት ወራት ውስጥ 1 ቢሊየን 356 ሚሊየን 119 ሺህ ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ግምታዊ ዋጋቸው 981 ሚሊየን 590 ሺህ ብር የሚገመት የገቢ ኮንትሮባንድ ለመያዝ ታቅዶ 1 ቢሊየን 100 ሚሊየን 631 ሺህ ብር የሚገመት ገቢ ኮንትሮባንድን ለመያዝ መቻሉ ታውቋል፡፡

ይህም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ24 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ነው የተባለው፡፡

በተመሳሳይ 134 ሚሊየን 708 ሺህ ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ወጪ ኮንትሮባንድ ለመያዝ ታቅዶ 255 ሚሊየን 487 ሺህ ብር ዋጋ የሚያወጡ ወጪ ኮንትሮባንድ የተያዘ ሲሆን ÷ አፈፃፀሙ 190 በመቶ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 107 ሚሊየን 276 ሺህ ብር ብልጫ አሳይቷል ነው የተባለው፡፡

በአጠቃላይ በአምስት ወራት ግምታዊ ዋጋቸው 1 ቢሊየን 116 ሚሊየን 298 ሺህ ብር የሆነ ወጪና ገቢ ኮንትሮባንድ ዕቃ ለመያዝ ታቅዶ ግምታዊ ዋጋቸው 1 ቢሊየን 356 ሚሊየን 118 ሺህ ብር የሆኑ ወጪና ገቢ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዝ መቻሉን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.