Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋን የመንገድ ሽፋን ሊያሳድጉ የሚችሉ አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች የዲዛይን ጥናት ስራዎች እየተከናወኑ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የመንገድ ሽፋን የሚያሳድጉና የተቀላጠፈ የትራፊክ ፍሰት የሚፈጥሩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን እንዲያስችል ታሳቢ የተደረጉ የማስተር ፕላን የመንገድ ዲዛይን ጥናቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ በተለያዩ አካባቢዎች መንገዶችን ለመገንባት በያዘው መሪ ዕቅድ መሰረት የከተማዋን የመንገድ ሽፋን ማሳደግ እንዲቻል ደረጃውን የጠበቀ የመንገድ ዲዛይን የሚሰራላቸውን መንገዶች ለይቶ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅትና የዲዛይን ጥናቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ ነው የጠቀሰው፡፡

በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በቀጣይ ወደ ግንባታ የሚገቡ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማስፈፀም የሚያስችለውን የማማከር አገልግሎትና የዲዛይን ጥናት ስራ ከሚያከናውኑ ስምንት አማካሪ ድርጅቶች ጋር ውል መግባቱንም አውስቷል፡፡

አጠቃላይ ብዛታቸው 99 የሆኑና ርዝመታቸው 255 ኪሎ ሜትር በላይ እና የጐን ስፋታቸው በአማካይ 20/60 ሜትር የሆነ የመንገድ ፕሮጀክት የዲዛይን ጥናት ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብሏል፡፡

የማማከር አገልግሎትና ዲዛይን ጥናት እየተከናወነባቸው ከሚገኙት ውስጥ የቀለበት መንገድ መልሶ ማልማት ግንባታ ጥናት ስራ መጠናቀቁን ገልጿል፡፡

ሁለት አደባባዮችን የማሻሻያ ስራ፣ በስድስት ጥምር የተካተቱ 72 ነባር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች እንዲሁም በ2013 በጀት ዓመት አማካሪ እንዲቀጠርላቸው የዝግጅት ስራ ላይ የሚገኙ 25 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች እና የተገነቡ መንገዶችን መረጃ የማሰባሰብ ስራዎች መሆናቸውንም ጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የከተማዋን የትራንስፖርት ሲስተም የማሻሻል፣ የከተማዋ የፍሳሽ መስመር የማሻሻል ስራ እና የፈጣን አውቶብስ ትራንስፖርት መስመር ስራን ጨምሮ 14 የዲዛይን ጥናትና የማማከር ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም አንስቷል፡፡

እነዚህ የዲዛይን የማማከር ስራዎች እንደተጠናቀቁ በቀጣይ ወደ ግንባታ ሂደት እንዲገቡ የሚያስችሉ ቀሪ ስራዎች እንደሚሰሩ መገለጹን ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.