Fana: At a Speed of Life!

የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ፍፁም ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍፁም አሰፋ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኡስማን ዲዩን ጋር ተወያዩ።

ውይይታቸው በኢትዮጵያ የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ ላይና በተለያዩ ዘርፎች በኮሚሽኑና በዓለም ባንክ በጋራና በትብብር ሊሰሩ በሚችሉ ሥራዎች ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ኮሚሽነር ዶክተር ፍፁም በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይሁንታን ያገኘው ሀገራዊ የ10 ዓመት ልማት ዕቅድ ሰነድ የዝግጅት ሂደትና ይዘት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም ዕቅዱ ከዚህ በፊት ከታቀዱት የሚለይባቸውን ነጥቦች አብራርተው በዕቅዱ ዝግጅትም የክልሎች፣ የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች፣ የምሁራን፣ የግሉ ዘርፍና የሌሎችንም ባለድርሻ አካላትን ተሣትፎና አስተዋፀኦ አስረድተዋል፡፡

ኡስማን ዲዩን በበኩላቸው ድርጅታቸው ከፕላንና ልማት ኮሚሽን ጋር በተለያዩ ዘርፎች በትብብር ለመሥራት ያለውን ፍላጐት መግለፃቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በቀጣይም  በጋራ ሊሰሯቸው የሚችሉ ተግባራትን በዝርዝር የተወያዩ ሲሆን በድህነት ቅነሳ፣ በመረጃና ዳታ ጥራት ማሻሻል፣ በክትትልና ግምገማ፣ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ላይ አብረው ለመስራት ተስማምተዋል።

ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለይተውና የትብብር ማዕቀፉን አዘጋጅተው ወደ  ሥራ ለመግባት ቀጣይ ውይይቶችን ለማካሄድም ነው የተስማሙት፡፡

 

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

 

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

 

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.