Fana: At a Speed of Life!

አቶ መላኩ አለበል ከጀርመን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 8 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር ጋር ተወያይተዋል።
የግብርናው ዘርፍ ለሀገሪቱ ዋና የኢኮኖሚ ምንጭ ቢሆንም በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የታገዘ ባለመሆኑ ሀገሪቱ ያላትን ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብት ያህል እየተጠቀመችበት ባለመሆኑ መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በፈረንጆቹ ከ2011 እስከ 2013 የዓለም ኢኮኖሚ በወደቀበት ወቅት የጀርመን ኢኮኖሚ ከሁሉም የዓለም ሀገራት የተሻለ ዕድገት እንደነበረው ያስታወሱት ሚኒስትሩ ለኢኮኖሚው ተከታታይ ዕድገት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪው የተሰጠው ከፍተኛ ተኩረት ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያም አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ከከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ጋር ተሳስረው በመስራት ለሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክቱትን ድርሻ ለማሳደግ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ በማዘጋጀት ላይ መሆኗን ገልፀዋል፡፡
ከ60 ዓመት በላይ ያገለገለውን የሀገሪቱን የንግድ ፖሊሲ በማሻሻል የወጪና ገቢ ንግዱ በተመጣጠነ መንገድ የሚሳለጥበትን መንገድ በመፍጠር በሚቀጥሉት 10 ዓመታት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሻሻል እየተሰራ ስለመሆኑ አስረድተዋል፡፡
ጀርመንና ኢትዮጵያ የቆየና የጠበቀ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ስለመሆናቸው ጂቲ ዜድ በኢትዮጵያ እየሰራ ያለው ስራ ዋና ማሳያ መሆኑንም አመላክተዋል።
አያይዘውም በጀርመን መንግስት እየተደረገ ስላለው የኢኮኖሚ፣ ትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ሌሎች መሰል ድጋፎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በትግራይ ክልል ስለተካሄደው ህግን የማስከበርና የህልውና ዘመቻ ሁኔታ ለአምባሳደሩ በማስረዳት በቅርቡ አካባቢውን መልሶ በማልማት በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች ወደ ቀደመ ስራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ ስለመሆኑም ልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን አውር በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ለምስራቅ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ አህጉር ሰላም ዕድገትና ብልፅግና መረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ያላት ሀገር በመሆኗ የጀርመን መንግስት ለኢትዮጵያ ልዩ ትኩረት እንዳለው መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.