Fana: At a Speed of Life!

የደራሲና ተዋናይ ተ/ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደራሲና ተዋናይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ስርዓተ ቀብር በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ የተለያዩ መፅሃፍትን የደረሱ ሲሆን በተለያዩ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይም በተዋናይነት ተሳትፈዋል።

ዛሬ ረፋዱን በብሄራዊ ቴአትር ቤት የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተካሄዷል፡፡

በርካታ ተውኔቶች ላይ የትወና ችሎታቸውን ያስመሰከሩት ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ አጫጭር ልቦለዶችና ግጥሞቻቸው በሩሲያኛ ተተርጉመው ታትመዋል፡፡

ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ መተከዣ (ግጥምና ቅኔ) ፣ ጥላሁን ግዛው፣ ዕቃው፣ የሺ፣ አባትና ልጆች፣ ላቀችና ደስታ፣ ተሐድሶ የተሰኙ ተውኔቶችን ደርሰዋል።

እንዲሁም የዑመር ኻያምን ልብወለዳዊ የሕይወት ታሪኩና ሩብ አያቶቹ የትርጉም መፅሃፍ ለአንባቢያን አድርሰዋል።

ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር እና ጥበባት ኮሌጅ ለበርካታ ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል።

በሐረርጌ በ1929 ዓ.ም የተወለዱት ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ በ84 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም ሞት የተለዩት፡፡

 

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.