Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ለ2 ሺህ 135 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ለ2 ሺህ 135 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።

ታራሚዎቹ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ባሳዩት ስነ ምግባር መሰረት ይቅርታ እንደተደረገላቸው የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ አስታውቋል።

በዛሬው ዕለት ይቅርታ ከተደረገላቸው መካከል 2 ሺህ 87ቱ ወንዶች ሲሆኑ  48ቱ ሴቶች  ደግሞ መሆናቸውን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ገልጿል፡፡

ተጠሪነቱ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር  የሆነው የይቅርታ ቦርድ  በየደረጃው በሚገኙ የይቅርታ፣ የእርቅና አጣሪ ኮሚቴዎች ተጣርቶና ተገምግሞ በክልሉ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በቀበው የይቅርታ ጥያቄ መሠረት  ይቅርታውን አፅድቋል፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.