Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለወጣቶች 5 ቢሊየን ብር የሚገመት የገበያ ትስስር ለመፍጠር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተለያዩ የስራ መስኮች ተደራጅተው ለሚንቀሳቀሱ ወጣቶች 5 ቢሊየን ብር የሚገመት የገበያ ትስስር ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና የበጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ገለጸ።

ከመዲናዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ 880 ወጣቶች በሀገራዊ ብልጽግና ላይ የጋራ ግንዛቤ መፍጠሪያ ውይይት ተካሂዷል ።

በውይይቱ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የወጣቶችና የበጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊው አቶ አብርሃም ታደሰ የመዲናዋን ወጣቶች ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ሃላፊው በዚህ ዓመት ለ280 ሺህ ወጣቶች ስራ ለመፍጠር ታቅዶ 141 ሺህ ያህል ወጣቶች ሥራ አግኝተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ 200 ሚሊየን ብር በመመደብ 28 ሺህ ወጣቶችን በአረንጓዴ ልማት ለማሳተፍ ስልጠና እየሰጠ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም በኩል 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ብድር መዘጋጀቱን ጠቅሰው 300 ሚሊየን ብር በሊዝ ፋይናንሲንግ በመመደብ የከተማዋን ወጣቶች ለመጥቀም መታቀዱን መግለፃቸውን ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት የተገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተለያዩ የስራ መስኮች ተደራጅተው ለሚንቀሳቀሱ ወጣቶች 5 ቢሊየን ብር የሚገመት የገበያ ትስስር እንደሚፈጠር ተናግረዋል።

በፖለቲካ ተሳትፎ የአስፈጻሚ ወጣቶች ምጣኔ 70 በመቶ መድረሱንና ይህንንም ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን አክለዋል።

የመዲናዋ ወጣቶች በማኅበራዊ ልማት ዘርፍ ከሚከውኗቸው ተግባራት መካከል የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቀዳሚ ነው።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.