Fana: At a Speed of Life!

በ100 ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢራናዊያን በአሜሪካ የተገደሉትን ወታደራዊ መሪያቸውን አስከሬን ተቀብለዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ100 ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢራናዊያን በአሜሪካ የሰው አልባ ጥቃት የተገደሉትን ወታዳራዊ መሪያቸውን ቃሴም ሱለይማኒን አስክሬን አደባባይ በመውጣት ተቀብለዋል፡፡

ኢራናዊያኑ በአህቫዝ እና በማሽሃድ አደባባዮች በመውጣት አሜሪካ ኢራቅ ውስጥ በፈፀመችው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የተገደሉትን  የኢራን ብሄራዊ አብዮት ዘብ ጠባቂ ሃይል አዛዥ ጀኔራል ቃሴም ሶሊማኒን  አስክሬን ተቀብለዋል፡፡

አስክሬኑን በተቀበሉበት ወቅት ኢራናዊያኑ ደረታቸውን እየመቱ ሀዘናቸውን የገለፁ ሲሆን  ሞት ለአሜሪካ የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡

አብዮት ዘብ ጠባቂ ሃይል አዛዡ ቃሴም ሶሊማኒ አስክሬን ከተገደሉ ሁለት ቀናት በኋላ  ነው በደቡብ ምስራቅ ወደ ምትገኘው አህባዝ ከተማ በዛሬው ዕለት አቅንቷል፡፡

ቃሴም ሶሊማኒ ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ለፈጠረችው ተፅዕኖ ከፍ ያሉ አስተዋፅኦ እንዳላቸው የሚነገር ሲሆን በኢራን ሁለተኛ ከፍተኛ ሀይል( ስልጣን) እንደነበሩም ይገመታል፡፡

የዚህ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳዳሪ ግለሰብ መገደል በኢራን እና አሜሪካ መካከል ያለውን ውጥረት ከፍ አድርጎ በቀጠናው ያለውን ቀውስ እንዳያባብሰው ተሰግቷል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራና ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.