Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከያቤሎ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ክልል በምትገኘው የቦረና ዞን ከያቤሎ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም የከተማዋ ነዋሪዎች የፍቅርና ሰላም እሴቶችን በአንድነት አጽንተው፣ ለኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት መሠረት እንዲያደርጓቸው አሳስበዋል።

የማኅበረሰቡ ሽማግሌዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት የታዩትን የሃይማኖትና ሌሎች ነጻነቶች ዋቢ አድርገው፣ ኢትዮጵያ እየተጓዘችበት የምትገኘውን የዴሞክራሲ ጎዳና አድንቀዋል።

በተጨማሪም የአካባቢውን የመሠረተ ልማት፣ የውኃ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፍላጎት እንዲሁም የአርብቶ አደሩን ማኅበረሰብ ፍላጎት ከማሟላት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ማንሳታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በተያያዘም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምዕራብ ጉጂ ዞን ከቡሌ ሆራ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ላይ የአካባቢው የሃገር ሽማግሌዎች ነዋሪዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.