Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ከአፋርና ከሲዳማ ክልል በሚዋሰንባቸው ወረዳዎች የየክልሎቹን ቋንቋዎች ለማስተማር ዝግጅት አጠናቋል- አቶ አዲሱ አረጋ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ከአፋርና ከሲዳማ ክልል በሚዋሰንባቸው ወረዳዎች የክልሎቹን ቋንቋዎች በትምህርት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ፡፡
በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ እንደገለፁት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከአፋር ክልላዊ መንግስት ጋር በሚያወስኑት የኦሮሚያ ወረዳዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የአፋርኛ ቋንቋን ለማስጀመር ዝግጅት ተደርጓል፡፡
እንዲሁ በተመሳሳይ ኦሮሚያ ከሲዳማ ክልላዊ መንግስት በሚዋሰንባቸው የኦሮሚያ ወረዳዎች ባሉ ትምህርት ቤቶች ደግሞ የሲዳሚኛ ቋንቋ ትምህርት ለማስጀመር ዝግጅት አጠናቀናል፡፡
አቶ አዲሱ እንደገለፁጽ አንዱ የሌላዉን ቋንቋ መማር የህዝቦችን በወንድማማችነት፣ እኩልነት እና በመከባበር የተመሰረተ መስተጋብር ያጎለብታል፡፡
ስራው ጠንካራ አንድነት ያላት ሀገርን ለመገንባትም ያግዛልም ብለዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.