Fana: At a Speed of Life!

የአድዋ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዛሬ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአድዋ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዛሬ መጀመሩ ተገለጸ።

በትግራይ ክልል በጁንታው ጉዳት ደርሶበት የነበረው የኤሌክትሪክ መስመር ተጠግኖ የአድዋ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልገሎት አግኝቷል።

መሠረተ ልማቱን ለመጠገን የፌዴራል መንግስት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት አብዛኞቹ የትግራይ አካባቢዎች የመብራት አገልግሎት እንዳገኙ መገለጹ ይታወሳል።

በጁንታው ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ሆኖ የቆየው የአድዋ የኤሌክትሪክ መስመር በመጠገኑ ከተማው የመብራት አገልገሎት ዛሬ አግኝቷል።

የአክሱም፣ ሽሬና ሑመራ ከተሞችም ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ከኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ሃይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.