Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ልዑክ ናይሮቢ ከሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የሶማሌ ክልል የኢንቨስትመንት እና ዳያስፖራ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልሰላም ዩሱፍ የተመራው የሶማሌ ክልል የልዑካን ቡድን በናይሮቢ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።
የልዑካን ቡድኑ በትናንትናው ዕለት በኢትዮጵያ ኤምባሲ በመገኘት በናይሮቢ ከሚኖሩ የሶማሌ የክልል ተወላጆች ጋር ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የኤምባሲው ምክትል ሀላፊ አምባሳደር ሲራጅ ረሺድ ባደረጉት ንግግር÷ የሶማሌ ክልል ተወላጆች ከኤምባሲው ጋር ተቀራርበው በመስራት በሃገር ልማት ላይ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል።
ይህንኑ ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.