Fana: At a Speed of Life!

በኪስማዮ ሴክተር ስድስት የተሰማራው የ5ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የተዋጊ መሃንዲሶችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኪስማዮ ሴክተር ስድስት የተሰማራው የ5ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ያሰለጠናቸውን የተዋጊ መሃንዲስ ሰልጣኞችን አስመረቀ፡፡

በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ የተሰጠው ስልጠና የተቀነባበሩ ፈንጅዎችን ማስወገድ ፣ በኮንቦይ እጀባ ወቅት የመንገድ ፍተሻ ማድረግ እና የተቀበረ ፈንጅን ማስወገድ በሚቻልበት አግባብ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡

የኡንማስ አገናኝ ኬቬን ኪዘላ እንደተናገሩት ስልጠናው በተሰማሩበት ግዳጅ ክህሎትና አቅም አግኝተው የሰራዊቱ ደህንነት እንዲጠበቅ ስልጠናው አጋዥ ነው ፡፡

የሻለቃው ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰፋ መኮነን በበኩላቸው ከግዳጅ ቀጠናው አንፃር የተሰጠው ስልጠና አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ሻለቃው ቀጣይ ለሚወጣው ግዳጆች የተመራቂዎች ሚና የጎላ ነው ማለታቸውንም ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የሻለቃው ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሌተናል ኮሎኔል ስንታየሁ ለታ ያልፈንዱ መሳሪያዎች ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት የማስወገድ ትምህርት መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

የተሰጠው ስልጠናውመ ሞያተኞቹ የነበራቸውን አቅምና ችሎታ የበለጠ ያጎለበቱበት ነው ብለዋል፡፡

የሻለቃው መሃንዲስ ሃላፊ ሻምበል እንግዳወርቅ ጌታነህ የተሰጠው ስልጠና የአልሸባብን እንቅስቃሴ ማዕከል ያደረገና ለሞያተኞቹ ትልቅ አቅም የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.