Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት ከ25 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት አመቱ ስድስት ወራት ከ25 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ የበጀት ዓመቱን የስድስት ወራት አፈፃፀም በሚመለከት ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሰጡት ማብራሪያም ባለፉት ስድስት ወራት ኩባንያው 25 ነጥብ 57 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቀዋል።

የተገኘው ገቢ ከተያዘው እቅድ የ95 በመቶ ስኬት የተመዘገበበት መሆኑን አብራርተው፤ እቅዱን ሙሉ ለሙሉ ማሳካት ያልተቻለው በአገሪቷ አንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ሳቢያ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህም ሆኖ የተገኘው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ12 ነጥብ 5 በመቶ እድገት አሳይቷል ብለዋል።

በተጠቀሰው ወራት የውጭ ምንዛሬ ግኝቱም 80 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የሞባይልና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር በየጊዜው እድገት እያሳየ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልጸዋል።

ከሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች መካከል 64 ነጥብ 3 በመቶው የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

እንደ ወይዘሪት ፍሬህይወት ገለፃ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 39 የተሻሻሉ ምርትና አገልገሎቶች ለደንበኞች ቀርበዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ ደንበኞች 50 ነጥብ 7 ሚሊዮን መድረሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.