Fana: At a Speed of Life!

የበሪሳ ጋዜጣ መስራች ፕሮፌሰር ማህዲ ሀሚድ ሙዴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የበሪሳ ጋዜጣ መስራች ፕሮፌሰር ማህዲ ሀሚድ ሙዴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

ፕሮፌሰር ማህዲ ሀሚድ በ1960ዎቹ በብቸኝነት በአፋን ኦሮሞ ሲዘጋጅ የነበረውን በሪሳ ጋዜጣን ካቋቋሙት እና በአርታኢነት ካገለገሉ ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ነበሩ፡፡

በሪሳ በጊዜው በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የአፋን ኦሮሞ የግል ጋዜጣ የነበረ ሲሆን በደርግ መንግስት ከተወረሰ በኋላም ብቸኛው በቋንቋው የሚታተም ጋዜጣ ነበር፡፡

የሂሳብና የፊዚክስ መምህሩ ፕሮፌሰር ማህዲ ሀሚድ ሙዴ የአፋን ኦሮሞ መዝገበ ቃላት፣ የበሪሳ ግጥሞች፣ የበሪሳ ደብዳቤዎችን እና ሌሎች መፅሀፍትን ለንባብ አብቅተዋል፡፡

ፕሮፌሰሩ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጭሮ ከተማ የተወለዱ ሲሆን ኑሯቸውን ውጭ ሃገር አድርገው ቆይተዋል፡፡

ባደረባቸው የልብ ህመም የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቢቆዩም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.