Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ጃፓን ለመንገድ ልማት 190 ሚሊየን ብር ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስትና የጃፓን መንግስት ለአስፋልት መንገድ ልማት የሚውል 190 ሚሊየን ብር የእርዳታ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ያስሚን ወሀብረቢና በኢትዮጵያ የጃፓን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ኢቶ ታኮ ፈርመዋል፡፡
ስምምነቱም በጃፓን መንግስት መደበኛ የልማት ፕሮግራም ማዕቀፍ ስር ከሚገኘው የኢኮኖሚና የማህበራዊ ልማት ትብብር አካል ሲሆን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ወደ ጂቡቲ እና ወደ በሱዳን የሚወስዱ ዋና ዋና መንገዶቸን ለማደስ ይውላል ነው የተባለው፡፡
በዚህ ውቅት ሚኒስትር ዲኤታዋ የሁለቱ ወዳጅ ሃገራት ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው እንደሆነ ገልፀው ድጋፉ በኢትዮጵያ ካለው ፈጣን የከተሞች መስፋፋትና የተሸከርካሪዎች ቁጥር መጨመር የተነሳ ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ለማሻሻል፣ ለተጓዡ ምቾትን ለመፍጠር እና በጉዞ የሚባክን ጊዜን ለማዳን ይረዳል ብለዋል፡፡
እንዲሁም የልማት ድጋፉ በየጊዜው የሚከሰተውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ እና የተሸከርካሪዎችን ከፍተኛ የነዳጅና የጥገና ወጪዎችን በማዳን በኢኮኖሚው ላይ ያለውን ጫና ለማቃለል እንደሚያግዝ ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በበኩላቸው የጃፓን የልማት ትብብር ትኩረት በዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በኢንዱስትሪ፣ በግብር፣ ከፍተኛ ጥራት ባላቸው የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እንዲሁም በትምህርት እና በጤና ዘርፎች መሆኑን መናገራቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.