Fana: At a Speed of Life!

የቻይናው ሻንግቴክስ ኩባንያ በ65 ሚሊየን ዶላር ወጪ በቦሌ ለሚ ሊሰማራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ሻንግቴክስ ሆልዲንግ ኩባንያ በ65 ሚሊየን ዶላር ወጪ በቦሌ ለሚ 2 ኢንዱስትሪ ፓርክ ሊሰማራ ነው።

ኩባንያው በፓርኩ መሰማራት የሚያስችለውን የኪራይ ስምምነት ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በዛሬው እለት ተፈራርሟል።

ኩባንያው በቦሌ ለሚ 2 ኢንዱስትሪ ፓርክ በ65 ሚሊየን ዶላር ወጪ በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ እንደሚሰማራ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ሌሊሴ ነሜ ገልፀዋል፡፡

ሻንግቴክስ በፓርኩ ውስጥ ስራ ሲጀምር ከ4 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.