Fana: At a Speed of Life!

ስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት አምባሳደር ተፈሪ ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር  ተፈሪ ታደሰ የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር  ቢያትሪስ ዋኒ ኖህ ጋር ተወያዩ።

ሚኒስትሯ ቢያትሪስ ዋኒ-ኖህ ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን እውነተኛ አጋር እንደሆነች በመግለፅ ይህ ደግሞ መንግስታት ቢቀያየሩም ሳይዋዥቅ ፀንቶ መቀጠሉን ገልፀዋል።

አምባሳደሩ በሁለቱ ዓመት የሥራ ጊዜያቸው ወቅት የሁለቱ ሀገራት መልካም ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ድርሻ ተወጥተዋል በማለት አመስግነዋቸል።

አምባሳደሩ በበኩላቸው ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ድንበር ከመጋራትም ባለፈ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው በመግለጽ ሁለቱን ሀገራት በመሠረተ-ልማት በተለይም ደረጃቸውን በጠበቁ አስፋልት መንገዶች ማስተሳሰር ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ፋይዳው ከፍተኛ በመሆኑ በቶሎ ሊተገበር ይገባል ማለታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በሁለቱ ዓመት የሥራ ጊዜያቸው ወቅት በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በኩል ለነበረው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።

ይህ መልካም ግንኙነት ከአዲሱ አምባሳደር ጋርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ጠንካራ እምነት ገልጸዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.