Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ የህዝቦችን ትስስር ለማጠናከር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው- አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ የህዝቦችን ትስስር ለማጠናከር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ ።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ክልል የህዝቦችን ትስስር ለማጠናከር ከአፋን ኦሮሞና አማርኛ በተጨማሪ በ3 የኢትዮጵያውያን ቋንቋ ትምህርት እንዲሰጥና አንዱ የሌላውን ባህል እንዲያዉቅ በዕቅድ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በመሠረተ ልማት ለማስተሳሰር ፣ ተቋማትን በጋራ በማጠናከርና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በጋራ ለመስራት ከአጎራባች ክልሎች ጋር በትብብር መስራት ተጀምሯል ብለዋል ።

እንዲሁም በክልሉ የመንግስት ሚዲያ በተለያዩ ቋንቋዎች ሥርጭት መጀመሩ ህዝቦችን ለማቀራረብ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

የሰሜንና ምዕራብ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የምክክር መድረክ  “መልካም ጉርብትና ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.