Fana: At a Speed of Life!

ከመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለመስጠት በግልገል በለስ ከተማ ጊዜያዊ ማዕከል መከፈቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በመተከል ዞን በተፈጠረው አለመረጋጋት የተፈናቀሉ ዜጎችን ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በግልገል በለስ ከተማ ጊዜያዊ ማዕከል መከፈቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
 
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ታረቀኝ ቴሲሳ የአስቸኳይ ጊዜ የአደጋ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል የተቋቋመበት ዋና ዓላማ ሰብዓዊ ድጋፍ ከማቅረብ ባሻገር ተፈናቃዮች ወደ ነበሩበት ቀዬ እንዲመለሱ ለማድረግ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
 
እንዲሁም ከፌዴራል እስከ ወረዳ የተቋቋመው ግብረ ኃይል በጋራ ስራውን በማከናወን በቅርበት ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
በአሁኑ ወቅት በመተከል ዞን 104 ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃዮች በ12 የመጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው እንደሚገኙ ተጠቅሷል፡፡
 
በዞኑ ሰባት ወረዳዎች ውስጥ ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፍ እየቀረበ ሲሆን በሁሉም ወረዳዎች የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አደጋ ምላሽ ማስተባባሪያ ማዕከል በኩል ስርጭቱ ተደራሽ እየተደረገ ነው ተብሏል።
 
የተፈናቃዮችን ሁኔታ በአራት ደረጃዎች የመደቡት ኮሚሽነሩ በ2011 ዓ.ም ተፈናቅለው የነበሩና ተመልሰው የተቋቋሙ ዜጎችን ድጋፍ ማድረግ፣ አሁን ላይ ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ላይ ያሉትን፣ በስጋት ወደ ጫካ ሸሽተው የነበሩ እና ተመልሰው ድጋፍ የሚሹ እና በቻግኒ ከተማ ራች መጠለያ የሚገኙ ዜጎችን ልዩ ትኩረት በመስጠት ከፌዴራል መንግስት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ መሆኑን ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።
 
የተቋቋመው ግብረ ሃይል ሰብዓዊ ድጋፎችን በማቅረብ እና ዜጎች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ እስከ መጋቢት 30/2013 ወደ ነበሩበት የማስመለስ ስራ ይሰራል መባሉን ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
 
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
 
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
 
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
 
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.