Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በመጭው ክረምት የሚተከል 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ችግኝ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በመጭው ክረምት በአረንጓዴ አሻራና በመደበኛው መርሀ ግብር የሚተከል 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ችግኝ እየተዘጋጀ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ እስመላለም ምህረት ÷ ችግኙ እየተዘጋጀ ያለው በመንግስት፣ በግልና በማህበር በተቋቋሙ ከ96 ሺህ በላይ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች እንደሆነ ገልፀዋል።

እንደ የአካባቢው ስነምህዳር ተስማሚ የሆኑ ችግኞችን በመለየት የዝግጅት ስራው እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል።

ችግኞቹ ለደን ልማት፣ ለእንሳሰት መኖ፣ ለፍራፍሬ ምግብነትና ለሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚውሉ የዛፍ ዝርያ አይነቶች መሆናቸውን የተናገሩት ተወካይ ዳይሬክተሩ እስካሁን 68 ሚሊየኑ ለተከላ በሚያበቃቸው ደረጃ ላይ ናቸው ነው ብለዋል።

እየተዘጋጁ ካሉት መካከል ዋንዛ፣ ወይራ፣ ኮሶና ዝግባ ሀገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች እንደሚገኙበት ጠቅሰው፤ ችግኞቹ 182 ሺህ ሄክታር መሬት የሚሸፍኑ መሆናቸውን የገለጹት አቶ እስመላለም፤ ባለፉት አመታት በተተከሉ ችግኞች የክልሉ የደን ሽፋን 14 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱን አስታውቀዋል።

በክልሉ ባለፈው ክረምት በመደበኛውና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከተተከሉ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ችግኞች 87 በመቶ መፅደቁን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.