Fana: At a Speed of Life!

የህወሀት የጥፋት ቡድን ላይመለስ ተደምስሷል- የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር ቀንዓ

የህወሀት የጥፋት ቡድን ላይመለስ ተደምስሷል- የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር ቀንዓ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሀት የጥፋት ቡድን ላይመለስ ተደምስሷል ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀንዓ ያደታ ገለፁ።

የመከላከያ ሚኒስትሩ በህወሀት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው በህግ ማስከበርና ህልውና ዘመቻው ወቅት ዕጅ ሰጥተው በደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል የተሃድሶ ስልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙትን የልዩ ሃይል እና የሚሊሻ አባላትን አወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም ደም መጣጩ ቡድን እናንተን እሳት ውስጥ ማግዶ ተደምስሷል ብለዋል፡፡

ህወሓት ለግል ጥቅሙ እና ለስልጣን ጥማቱ ሲል እኩይ ተግባራትን በኢትዮጵያውያን ላይ ፈጽሞ ላይመለስ ተወግዷል  ነው ያሉት፡፡

ሰልጣኞቹ  በውሸት ወሬ ሳይረበሹ ስልጠናቸውን በማጠናቀቅ ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው መመለስ እንዳለባቸው ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

የህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራል ሀሰን ኢብራሂም በበኩላቸው÷ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከጁንታው ጋር የተሰለፉ ዜጎችን ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል ፡፡

እጅ የሰጡት አባላት በበኩላቸው ግዴታ ሆኖባቸው ቢሰለፉም ምንም ሳይተኩሱ እጃቸውን ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ የመከላከያ ሰራዊት ጥሩ እንክብካቤ እያደረገላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

በቀጣይ ለሃገራቸው ሰላም በጋራ እንደሚቆሙ መናገራቸውንም ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

እጅ ሰጥተው በደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል የተሃድሶ ስልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙት 764 ዜጎች ናቸው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.