Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጋር በመዲናዋ አዲስ አበባ እና በቻይና መካከል እየጠነከረ ስለመጣው ዘርፈ ብዙ ግንኙነት እና ትብብር ተወያዩ፡፡

ምክትል ከንቲባዋ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት የመዲናዋ ገጽታ፣ ማህበራዊ አኗኗር እና ኢኮኖሚ በማሻሻል ረገድ ትልቅ ፋይዳ ስለሚኖረው የአዲስ ፕሮጀክት እና ሌሎች የመንገድ እንዲሁም የመሰረተ ልማት ፕሮጀችቶች ጥራት እና የአፈጻጸም ፍጥነትን ማሻሻል ስለሚቻልበት ዙሪያ መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ በነበራቸው ቆይታ አምባሳደሩን እና የስራ ባልደረቦቻቸው አመሰግነዋል፡፡

በመጨረሻም አዲስ አበባ ለኑሮና ለስራ አመቺ፣ “እንደስምዋም ውብ የማድረግ ስራችንን አጠናክረን እንደምንቀጥል ላረጋግጥ እወዳለሁ” ሲሉ አስፍረዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.