Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ሚኒስቴር ከዲቦራ ፋውንዴሽን ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የትምህርት ሚኒስቴር እና ዲቦራ ፋውንዴሽን በትምህርት ዘርፉ ላይ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በመግባቢያ ሰነድ ፊርማው ላይም የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ስምምነቱ አካታች ሁሉን አቀፍ እና ፍትሃዊ ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ እና ዘላቂ የትምህርት እድል ለመፍጠር የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ ዓላማ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ሕፃናትን ለማስተማር የሚያስችል የመምህራን የሥልጠና መርሃ ግብር እንዲኖር ለማድረግ እና ሁሉን አቀፍ ጥራት ያለው ትምህርት አቅርቦት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ ያለመ መሆኑም በስምምነቱ ተገልጿል፡፡

ለመንግስት ትምህርት ቤቶች እና ለመምህራን የአጭር ጊዜ የስልጠና መርሃግብሮችን በማዘጋጀት የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ላለባቸው ልጆች ሕክምና ለመስጠት የሚያስችል ሥልጠናና ትምህርት ለመስጠት መታሰቡንም በስምምነቱ ተነስቷል፡፡

ስምምነቱም የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ላለባቸው ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁሶች አቅርቦት እና ስርጭት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ እና የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ላለባቸው ልጆች የትምህርት መብትን ለመደገፍ እንደሚያስችል ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.