Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ውድድር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ውድድር ተጠናቋል፡፡

ላለፉት ወራት በአዳማ እና በሐዋሳ ከተማ የኮቪድ የውድድር ስርዓትን ጠብቀው ሲካሄዱ የነበሩት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 1ኛ እና 2ኛ ዲቪዚዮን ውድድሮች በዛሬው እለት በተደረጉ ጨዋታዎች ተጠናቀዋል፡፡

በሐዋሳ ከተማ ሲካሄድ የነበረውን ውድድር የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እና ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እና የሴቶች እግር ኳስ ልማት እና ውድድር ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሶፊያ አልማሙን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ እና የህክምና ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሀፊ እና የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አመራሮች በሐዋሳ ስታዲየም በመገኘት ውድድሩን ተከታትለዋል::

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውድድሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም የእውቅና የምስክር ወረቀት የሰጠ ሲሆን፤ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር ውድድሩ የተሳካ እንዲሆን ላደረጉ አካላት በሙሉ በስፖርት ኮሚሽን ስም አመስግነዋል፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የጸጥታ አካላት እና የሚዲያ አካላት ማመስገናቸውን ከኢትዮጲያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.