Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ለ29 ሺህ በላይ ልጃገረዶች የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት ማድረስ መቻሉን ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ29 ሺህ በላይ ልጃገረዶች የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት ማድረስ መቻሉን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

ወ/ሮ አዳነች በ2013 ዓ.ም 49,093 ለሚሆኑ ልጃገረዶች የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት ለመስጠት መታቀዱን ገልጸዋል።

እስካሁንም ለ29, 951 ልጃገረዶች ክትባቱን መስጠት መቻሉን አመላክተዋል፡፡

ሴቶችን እና 14 ዓመት የሆናቸውን ልጃገረዶች የሚያጠቃውን የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ለመከላከል ክትባቱ ከጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶችና በጤና ተቋማት በመሰጠት ላይ መሁኑን ነው ያነሱት።

እንደሚታወቀው በዓለም አቀፍ ደረጃ ብሎም በሀገራችን የማህጸን ካንሰር በሽታ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ በየዓመቱ የብዙ ሴቶችን ህይወት እየቀጠፈ የሚገኝ በሽታ ነው፡፡
በቀጣይም ይህንን ክትባት አንዲትም ልጃገረድ ሳትቀር መውሰድ ስለሚገባት ምክትል ከንቲባዋ አሳስበዋል።

የክትባት መስጫ ጊዜው እስከ ጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንዲሚቀጥል ገልጸው ፣ ወላጆች ይህንን በቀላሉ ክትባት በመስጠት መከላል የሚቻለውን ገዳይ በሽታ በመመከት ህይወት እንዳይቀጥፍ በጊዜ ልጆቻቸውን እንዲያስከትቡ መልእከት አስተላልፈዋል።

ይህ ክትባት ልጆቹ ጋር እንዲደርስ ትልቁን ድርሻ እየተወጡ ለሚገኙ ወላጆች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ መምህራን፣ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.