Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ መርህን መሰረት ያደረገ የእዳ አስተዳደር ስርአት እየተከተለች ነው – የገንዘብ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ መርህን መሰረት ያደረገ የእዳ አስተዳደር ስርአት እየተከተለች መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ዓለም አቀፍ የብድር አስተዳደር ስርአትን በተመለከተ እየተገበረ ባለው አሰራር ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫውም አሁን ላይ ኢትዮጵያ መርህን መሰረት ባደረገ መልኩ የእዳ አስተዳደር ስርአት እየተከተለች መሆኑን አስታውቋል፡፡

በመግለጫው ኢትዮጵያ ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ በቡድን 20 ሃገራት የብድር አገልግሎት ማዕቀፍ አማካኝነት ከዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሟን አስታውሷል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ ሃገራዊ የአኮኖሚ ማሻሻያውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የኮቪድ19 ተፅዕኖን ለመቋቋም ያለመ መሆኑንም ጠቅሷል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የእዳና የብድር ጫና የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

አሁን ላይም ያለውን የእዳ ዘላቂነት ግምገማ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አማካኝነት እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

ከዚህ ባለፈም በቀጣይ ከአበዳሪዎች ጋር ለሚደረገው ውይይት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ነው ያስታወቀው፡፡

ሚኒስቴሩ የእዳ አስተዳደር ስርአቱ የሃገሪቱን የእዳ ተጋላጭነት በመፍታት ተጨማሪ የእድገት አማራጮችን ያመጣል የሚል እምነት እንዳለውም ነው የገለጸው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.