Fana: At a Speed of Life!

ጃፓን በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍና መልሶ የማቋቋም ሂደቱን ለመደገፍ ዝግጁ ናት – በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃፓን በትግራይ ክልል ከተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ጋር በተያያዘ የሰብአዊ ድጋፍና መልሶ የማቋቋም ሂደቱን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮን ተናገሩ፡፡

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ክብርት ኢቶ ታካኮ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ሚኒስትሯ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ሂደት በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በዚህም በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍና ክልሉን መልሶ ለማቋቋም እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ለአምባሳደሯ ገልጸውላቸዋል፡፡

አምባሳደር ታካኮ በበኩላቸው ጃፓን በቀውስ ጊዜ ስራ አስተዳደር ሰፊ ልምድ ያላት ሀገር መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሂደቱን አስፈላጊ በሆነ መስክ ሁሉ ለመደገፍ መንግስታቸው ያለውን ፍላጎትና ዝግጁነት መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይም ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕን ጋር የተወያዩ ሲሆን፥ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሂደትን በተመለከተ ለአምባሳደሯ አብራርተዋል።

አምባሳደር አልፕ በበኩላቸው የሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሂደቱን ለመደገፍ የቱርክ መንግስት ያለውን ቁርጠኛ ፍላጎትና ዝግጁነት ገልጸዋል፡፡

የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለውን የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.