Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ ከዓለም ምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ስቴቨን ኦማሞ ጋር ተወያዩ፡፡

ሚኒስትሯ የዓለም የምግብ ድርጅት ኢትዮጵያ ቀውስ ባጋጠማት ወቅት ሁሉ ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጎን በመቆም ላደረጉት የረጅም ዘመናት ትብብር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የህግ ማስከበር ሂደቱን ተከትሎ በትግራይ ክልል ላጋጠሙ የሰብዓዊና የመሰረተ ልማት ቀውሶች አስቸኳይ ምላሽ ለመስጠት እየተካሄደ ስላለው አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ የማቋቋም ሂደት ገለጻ አድርገዋል።

የዓለም ምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ስቴቨን ኦማሞ በበኩላቸው የዓለም ምግብ ድርጅት እንደሁልጊዜውም ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጎን በመቆም የሰብዓዊ ድጋፍ ሂደቱን በተቀላጠፈ መንገድ ለማሳለጥ ከብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አማራር ኮሚሽን ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም በኢትዮጵያ መንግስት የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የተለዩ ጉዳዮች ላይ በቅንጅት ለመስራት ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.