Fana: At a Speed of Life!

አያት አደባባይ አካባቢ በሱቆች ላይ የተነሳው እሳት ወደ ሌሎች ሳይስፋፋ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት 3:00 ላይ አያት አደባባይ አካባቢ በሱቆች ላይ የተነሳው እሳት ወደ ሌሎች ሳይስፋፋ በቁጥጥር ስር ውሏል ።

በሱቆች ላይ የተነሳው የእሳት አደጋ በተደረገው ፈጣን ከፍተኛ ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል።

የእሳት አደጋው ወደ ሌሎች ሱቆች እንዳይዛመት የእሳት እና አደጋ መከላከል ሰራተኞች ፣የአካባቢው ማህበረሰብ እና የጸጥታ አካላት ላደረጉት ርብርብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምስጋና  አቅርቧል ።

ህብረተሰቡ ተመሳሳይ  ችግሮች  እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ  በማድረግ  አካባቢውን እንዲጠብቅ ከተማ አስተዳደሩ  ጥሪ ማቅረቡን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.