Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ በነገው ዕለት መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ  ስብሰባው ነገ ይካሄዳል፡፡

ምክር ቤቱ  በጠቅላይ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ  በሚያካሄደው መደበኛ ስብሰባው  በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

በዚህም ምክር ቤቱ የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ መንግስት እና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም  እንዲሁም  ለሴቶች ኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ፕሮጄክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ነው የሚጠበቀው፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በዳንስኬ ባንክ ኤ.ስ መካከል ለብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የሜቲዎሮሎጂ ምልከታ መሰረተ ልማት እና የትንበያ አቅም ግንባታ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያፀድቃል።

እንዲሁም የምርጫ ጉዳዮች በፍርድ ቤት የሚስተናገዱበት የሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ረቂቅ ደንብንም መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሏል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.