Fana: At a Speed of Life!

የትራፊክ አደጋን በሚጠበቀው መጠን መቀነስ አለመቻሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የትራፊክ አደጋ በሚጠበቀው መጠን ባለመቀነሱ በትኩረት እንዲሰራ አሳስቧል፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣንን የ2013 በጀት ዓመት የሁለተኛ ሩብ የዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡
የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣ የወጪና ገቢ ንግዱን በማፋጠን፣ የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ በማስገጠምና የመንገድ ዳር ምልክቶችንና ማመላከቻዎችን በመትከል ጥሩ አፈጻጸም እንደነበረውና በቀጣይም አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ቋሚ ኮሚቴው አመላክቷል፡፡
በሌላ በኩል የፕሮጀክቶች አፈጻጸም መጓተት፣ የትራፊክ አደጋን በሚጠበቀው መጠን አለመቀነስ፣ በአዲስ አበባ እና በሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት ዘርፍ ያለው እንግልትና የተሽከርካሪዎች ከደረጃ በታች መሆን እንዲሁም፤ ሞዴል የአሽከርካሪ ብቃት ማሰልጠኛዎችን ማብቃት ላይ የሚታዩ ጉድለቶችን በተመለከተ አስተያየት ተሰጥቷል፡፡
የትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ያደታ፤ የተጓተቱ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ከወሰን ማስከበርና ተያያዥ ችግሮች ጋር ያለው ችግር ተቀርፎ በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቁ ገልጸዋል፡፡
የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ከባለፈው 6 ወር አፈጻጸም አንጻር የተሻለ ቢሆንም የአሽከርካሪዎችን ባህሪ ለመለወጥ የሚያስችል ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ ስርዓተ ትምህርቱ ውስጥ ገንቢ ይዘቶችን በማካተት ዘላቂ የትውልድ ግንባታ ስራ እየተሰራ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ መናገራቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.