Fana: At a Speed of Life!

በካናዳ የነጭ የበላይነት አቀንቃኝ የሆነው ፕራውድ ቦይን ጨምሮ 13 ቡድኖች በሽብርተኝነት ተፈረጁ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ካናዳ የነጭ የበላይነት የሚያቀነቅነውን ፕራውድ ቦይን በሽብርተኝነት ፈረጀች።

ካናዳ ይህን ቡድን ጨምራ አራት የቀኝ አክራሪ ቡድኖችን በሽብርተኝነት መፈረጇን በዛሬው ዕለት አስታውቃለች።

በዚህም አቶምዋፈን ዲቪዥን ፣ ቤዝ ፣ የሩሲያ ኢምፔሪያል ንቅናቄን ጨምሮ 13 ቡድኖች በካናዳ የፌደራል መንግስት በሽብርተኝነት ተፈርጀዋል።

በመሆኑም በሽብርተኝነት የተፈረጁት ቡድኖች በካናዳ መንቀሳቀስ የማይችሉ ሲሆን ንብረቶቻቸውም ሊወረሱ እንደሚችሉ ግሎባል ኒውስ ዘግቧል።

የነጭ የበላይነት አቀንቃኙ ፕራውድ ቦይ ቀኝ አክራሪ እና ኒኦ ፋሽዝምን የሚያቀነቅን በአሜሪካ እና ካናዳ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው።

በቅርቡ በአሜሪካ ካፒቶል ሂል ከነበረው ሁከት ጋር በተያያዝ ስሙ ሲነሳ የነበረው ቡድኑ ለቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ድጋፍ እንዳለው ይነገራል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.