Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የህግ ማሻሻያ ሰነድ ዝግጅት ሂደትን የሚያሳይ  መጽሐፍ  ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መጽሐፉ የዝግጅት ምዕራፉን አጠናቆ ለንባብ መብቃቱ በኢትዮጵያ ሲደረግ የነበረውን የህግ ማሻሻያ ሂደት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ እና የህግ ጥናትና ምርምር ሥራዎችን ለመደገፍ ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

በመጽሐፉ የምረቃ ሥነ-ስርዓት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የፍትሐብሄርና ልዩ ልዩ ወንጀሎች ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ገለታ ስዩም ÷ የመጽሐፉ መዘጋጀት በሕግ ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ እና ወቅቱ የሚጠይቀውን ፍትህ የማስፈን ሂደት ለመደገፍ ብሎም በዘርፉ ዙሪያ ለሚደረጉ የጥናትና ምርምር ሥራዎች  እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

ቀጣዩ ትውልድ በአሁኑ ወቅት ሲደረጉ የነበሩ የሕግ ማሻሻያ ሥራዎችን በአግባቡ እንዲረዳ ከማድረግ አፃርም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ነው ያሉት፡፡

አይዘውም መጽሐፉ ተዘጋጅቶ ለንባብ እንዲበቃ የገንዘብና የሙያ ድጋፍ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በዋናነትም መጽሐፉ የሽብር፣የበጎ አድራጎት ማህበራት፣ የመገናኛ ብዙኃን ፣ የጦር መሣሪያ አስተዳደር እና ሌሎች ስምንት አዋጆችን እንዲሁም ሁለት የህግ መድብሎችን ማለትም የወንጀል ሰነ-ሥርዓትና የማስረጃ ህግ እንዲሁም የንግድ ህግን በተመለከተ ለማሻሻል መንግስት የወሰደውን እርምጃ በተመለከተ ማብራሪያ መሰጠቱን ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.