Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው የመስተዳድር ምክር ቤቱን ውይይት በቪዲዮ ኮንፍረንስ መርተውታል፡፡

የመስተዳድር ምክር ቤቱም በሁለት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ከዚህ ቀደም ሲነሱ የነበሩ የከተሞች የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ከጥናት በኋላ በምክር ቤቱ ምላሽ እንደተሰጠባቸው ተሰምቷል፡፡

ለብዙ ጊዜያት የከተሞች ህዝብ ሲያነሳቸው የነበሩ የከተሞች የፈርጅ ለውጥ ጥያቄን ጥልቅ ጥናት ተደርጎበትና መስተዳድር ምክር ቤቱ ሰፊ ውይይት አድርጎበት ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ከተሞቹ ወደ ፈርጅ 3 ከተማ አስተዳደር እንዲያድጉ መደረጉ በከተሞች መካከል ጤናማ የሆነ የውድድር መንፈስ በመፍጠር በሂደቱም የነዋሪውን የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ፣ ከተሞች ከደረሱበት የእድገት ደረጃቸው አንፃር በመፈረጅ እየተመዘገበ ያለው እድገት ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም በከተሞች የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ በማድረግ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ብሎም ከተሞች የገበያ፣ የአገልግሎት፣ የቴክኖሎጂ፣ የቱሪዝም እና የትምህርት ማእከላት በመሆን ለአካባቢያቸው የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማእከል የመሆን ሚናቸውን እንዲጫወቱ ለማስቻል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል በቀረቡ በኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ላይ መስተዳድር ምክር ቤቱ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ 33 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን አጽድቋል፡፡

በዚህም በአገልግሎት ዘርፍ ሶስት በግብርናው ዘርፍ 15 እንዲሁም በኢንዱስትሪው ዘርፍ 16 ፕሮጀክቶችን መርምሮ ማጽደቁን ከክልሉ መንግስት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.