Fana: At a Speed of Life!

በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተጎዱ ሠራተኞችን ለመደገፍ የ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተጎዱ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ዘርፍ የሚሰሩ ሠራተኞችን ለመደገፍ የ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ፡፡
ድጋፉ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የስራ ድርጅት ጋር በመተባበር በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተፅዕኖ ውስጥ የገቡ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንተርፕራይዝ ሠራተኞችን ለመደገፍ የሚያስችል ነው።
የገንዘብ ድጋፉ ከጀርመን መንግስት የኢኮኖሚ ልማትና የትብብር ሚኒስቴር የተገኘ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፥ ፕሮጀክቱ ዜጎች ስራቸውን እንዳያጡና ማህበራዊ ቀውስ እንዳይከሰት በማድረግ ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
የጀርመን ኤምባሲ የልማትና ትብብር ምክትል ኀላፊ ክሪስቶፎር ዌይጌለሜየር በበኩላቸው ድጋፉ የሁለቱን ሀገራት ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ወረርሽኙ በኢንተርፕራይዞች ላይ የፈጠረውን ተጽእኖ ለመግታት አስተዋጽኦ ይኖረዋልም ብለዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.