Fana: At a Speed of Life!

የሀላባ እና ካፋ ዞን ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የሀላባ ዞን ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያላቸውን ድጋፍ በሰልፍ ገለፁ፡፡

ነዋሪዎቹ ጁንታውን የማፍረሱ ድል የጋራ ጥረት ውጤት ነው ብለዋል።

አደናጋሪ አሉባልታዎችን በማክሸፍ ለለውጡ ዘላቂነት እንተጋለን፤ ለውጡን የሚያደናቅፍ የሴራ ፖለቲካ እናወግዛለን፤ ፈተናዎችን በጋራ እየመከትን የለውጡን ዘላቂነት እናረጋግጣለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን የሚያደናቅፉ የውስጥና የውጭ ሀይሎችን እናወግዛለን የሚሉ መፈክሮችንም አሰምተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ታላቁ የለውጥ ጉዞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መሪነት ተጠናክሮ ይቀጥላል የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች አንግበው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና በሚመሩት መንግስት እየተመዘገበ ላለው ስኬት ህዝባዊ እውቅና ሰጥተዋል።

በተያያዘም የካፋ ዞን ነዋሪዎች ለሃገራዊ ለውጡና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያላቸውን ድጋፍ በቦንጋ ከተማ ተገኝተው ገልጸዋል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ በሃገሪቱ እየተመዘገበ ያለውን የለውጥ ተግባር የሚያደንቁ ሃሳቦች ተንጸባርቀዋል፡፡

ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅ ከመንግስትና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስተዳደር ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።

ከዚህ ባለፈም ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በሃገሪቱ ለተመዘገበው ውጤት ዕውቅና ሰጥተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.