Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ኡመር እና ም/ር/መ አቶ ኢብራሂም በምዕራብ ጎዴ የስንዴ ሰብል ምርትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በግብርና ሚኒስቴር ሚንስትሩ አቶ ኡመር ሁሴን የተመራ ሉኡካን ቡድን እና በሶማሌ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን በምዕራብ ጎዴ የስንዴ ሰብል ምርትን ጎብኝተዋል።

በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሙከራ በምዕራብ ጎዴ በዋቢ ሸቤሌ ወንዝ በመስኖ እየለማ የሚገኘው የስንዴ ሰብል በተለያዩ የክልሉና የፌደራል ተቋማት በጋራ የሚለማው ይህ ፕሮጀክት በ500 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው ተብሏል፡፡

አቶ ኢብራሂም ኡስማን እየተሰራ ያለው ስራ ጅምር ቢሆንም በቀጣይ እስከ 50 ሄክታር በመስኖ ለማልማት መታቀዱን ገልጸዋል።

የሸቤሌ ወንዝን በመስኖ በማልማት ስንዴን ማምረት እንደሚቻል ፕሮጀክቱ ማሳያ እንደሆነም አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ የስንዴ ምርትን ከውጪ ለማስቀረት ባለፉት 57 ዓመታት ትልቅ ጥረት ማድረጓን ያስታወሱት የግብርና ሚኒስተሩ አቶ ኡመር ሁሴን ከለውጡ ወዲህ መንግስት ትኩረት ሰጥቶበት እየሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

ሚንስትሩ አክለውም ኢንቨስተሮች በክልሉ በሚተገበሩ የመስኖ ልማት ስራዋች ተሳትፎ እንዲያደርጉም ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ብዙኀን መገናኛ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.