Fana: At a Speed of Life!

በሐዋሳ ከተማ በአላሙራ ተራራ ላይ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በአካባቢው ህብረተሰብ ርብርብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሐዋሳ ከተማ አላሙራ ተራራ ላይ ለጌዜው መንስኤው ባልታወቀ ምክንያት ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በአካባቢው ህብረተሰብና በፀጥታ አካላት ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ፡፡
የእሳት አደጋው ምሽት 7 ሰዓት አካባቢ መቀስቀሱን የገለፁት የታቦር ክፍለከተማ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ፍቅሬ እስከ ንጋት ቀጥሎ በአካባቢው ነዋሪዎች ርብርብ ወደሌላ አካባቢ ሳይዛመት እና የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
የአደጋው መንስኤና በአካባቢው ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን ተጣርቶ የሚገለፅ መሆኑንም አመላክተዋል።
የእሳት አደጋው በህብረተሰቡ ርብርብ በቁጥጥር ስር ባይውል የከፋ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል የገለፁት አቶ ታደሰ ለአካባቢው ነዋሪዎች እና ለፀጥታ አካላት አደጋውን ለመቀነስ ላደረጉት ርብርብ ምስጋና አቅርበዋል።
ወቅቱ ነፋሻማ እና ሞቃት እንደመሆኑ መጠን የእሳት መቀጣጠልና የመስፋፋት ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑ ገልፀው ህብረተሰቡ የጥንቃቄ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.