Fana: At a Speed of Life!

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ልዑክ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመወያየትና ድጋፍ ለማድረግ ወደ ትግራይ ክልል አቀና

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶችን ፣የሀገር ሽማግሌዎችንና መማክርትን ያካተተ ልዑክ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመወያየትና ድጋፍ ለማድረግ ወደ ትግራይ ክልል ማቅናቱን የጉባኤው ዋና ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ገለጹ።

ከዛሬ  ጀምሮ ለሦስት ቀናት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶችን ፣የሀገር ሽማግሌዎች መማክርትን ያካተተ ልዑክ ወደ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ማቅናቱ ነው የተጠቀሰው።

ልዑኩ በሚኖረው ቆይታ  በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከህብረተሰቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚወያይም ነው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ  ዋና ጸሐፊው ለኢዜአ ገልጸዋል።

ልዑኩ በሚኖረው ቆይታ በተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችንና ፣በተለይም በቤተ እምነቶች ላይ በደረሰው ጉዳት ዙሪያ እንደሚመክር ተናግረዋል።

በተጨማሪም ልዑኩ በቀጣይ ምን መሠራት እንዳለበት ከአከባቢው የእምነት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች ፣እንዲሁም ከመንግሥት እና ከጸጥታ አካላት ጋር ምክክር ይደረጋል ብለዋል።

የጉባኤው አባል የሆኑት የሐይማኖት ተቋማትም የድጋፍ ስራዎችን እንደሚያከናውኑና በአሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገረ ስብከቶችን የሚመሩ ሊቃነ ጳጳሳት በኦን ላይን ያሰባሰቡት ድጋፍም ለህበረተሰቡ እንደሚለገስ ዋና ጸሐፊው ገልጸዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.