Fana: At a Speed of Life!

ቋሚ ኮሚቴው የአካባቢ ጸጋዎች የስራ እድል መፍጠሪያ ሊሆኑ እንደሚገባ ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአካባቢ ጸጋዎች የስራ እድል መፍጠሪያ ሊሆኑ እንደሚገባ ገልጿል፡፡
ኮሚቴው የፌደራል የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራ እና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲን የ2013 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረመስቀል ጫላ የስራ ፈጠራ መፈልፈያ ማዕከላት ለማቋቋም በማቀድ በግማሽ አመቱ የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ በየክልሉ ሊከፈቱ የሚችሉ ማዕከላትን መለየት ተችሏል ብለዋል፡፡
እንዲሁም አዳዲስ የስራ አማራጮችን በጥናት በመለየት ስድስት ሞዴል የንግድ እቅድ በማዘጋጀት ለክልሎች ማሰራጨታቸውን ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል ተዘዋዋሪ ብድር ፈንድ ለማስመለስ ግብረ ሃይል አደራጅተው እየሰሩ መሆናቸውን አንስተው ይህንን ችግር ከመሰረቱ ለመቅረፍ አዋጭ ላልሆነ ቢዝነስ ፕላን ብድር መሰጠት እንደሌለበት አመላክተዋል ፡፡
በዚህም ቋሚየጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ባንክ እና የስራ ፈጠራ ማጎልበቻ ማዕከላት ለማቋቋም እንዲሁም ከቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ለስራ ፈላጊዎች ገበያ ተኮር ስልጠና መሰጠቱን በጥንካሬ ተመልክቶታል፡፡
በሌላ በኩል የመንግስት ድጋፎችን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር የመስሪያ እና መሸጫ ሼዶችን ለመገንባት እና መሰረተ-ልማት ለማሟላት፣ ብድር ለማቅረብ፣ የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለመስጠት እና የገበያ ትስስር ለመፍጠር የተደረጉ ድጋፎች ትኩረት የሚሹ መሆናቸውን አመላክቷል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አሸናፊ ጋኢሚ በበኩላችው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ባንክ ለማቋቋም እየተሰራ ያለውን ስራ በጥንካሬ አንስተው ነገር ግን ኤጀንሲው የአከባቢ ጸጋዎችን የስራ ዕድል መፍጠሪ አማራጭ አድርጎ ከመጠቀም አኳያ ያሉ ውስንነቶችን ቀርፎ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ መናገራቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.